የስኳር በሽታ diabetes

ቤተሰብና ጓደኞች የስኳር በሽታን ጉዳይ ለመቆጣጠር
ተባብረው በየጊዜው እንቅስቃሴ (ስፖርት) በማድረግና
ጤና ምግብም በመምረጥ ሕመምተኛውን ለመርዳት
ይችላሉ።
ስኳር በሽታን ለመቆጣጠር እንቅስቃሴ (ስፖርት)
በጣም ጠቃሚ ነው። በሳምንት ቢያንስ ሦስቴ ለ 30
ደቂቃ ያህል ወንድ፣ ሴት፣ ልጅ፣ ኣዋቂ፣ ሳይሉ
ሁሉም ስፖርት መሥራት ያስፈልጋል። ይኸውም
የእግር ኳስ፣ የእጅ ኳስ፣ የባስኬት-ቦል፣ የገመድ
ዝላይ፣ ደረጃ መውጣት፣ ወይም ከቤተሰብ ጋር
የእግር ሽርሽር ጉዞ በመሄድ ናቸው።

የስኳር በሽታ ካለብዎት ማድረግ የሚገባ፦
· ሓኪም ያዘዘውን መድሓኒት በጥንቃቄ
መከታተል
· የደም ስኳር ብዛት በየጊዜው መለካትና
መቆጣጠር
· ስም፣ ኣድራሻ፣ ሕመምዎንና፣ መድሓኒቶችዎን
የሚነግር መታወቂያ መያዝ።
· ምቹ የሆነ ልብስና ጫማ ማድረገ
· ብዙ ውሃ መጠጣት
· እንቅስቃሴና ስፖርት ማዘውተር
· ከረሜላ፣ የፍራፍሬ ጭማቂ፣ ዘቢብ፣
የመሳሰለውንም ጣፋጭ ነገሮች ይዞ መሄድ
ያስፈልጋል፣ ምክንያቱም ስኳርዎ ዝቅ ቢል
መጠባበቅያ እንዲሆን።

የስኳር በሽታ ሰውነት ኢንሱሊን የተባለውን ቅመም
ሳይሠራ ሲቀር ነው። ኢንሱሊን በሰውነት የሚገኝ
ቅመም (ሆርሞን) የምንበላው ምግብ ኃይል እንዲሆነንና
ኣካላታችን ጉልበት ኣግኝቶ እንዲሠራ የሚያደርግ
ነው። የስኳር በሽታ በደም ውስጥ ያሚገኘውን ስኳር
ከሚገባው መጠን እጅግ ከፍ እንዲል ካደረገው፥
ልብ፣ ኣንጐል፣ ኩላሊት፣ የደም-ስሮች፣ ጥርሶች
ሊጎዱ ይችላሉ። የስኳር በሽታ የዓይን መታወርን፣
የግብረ-ስጋን ተግባር መዳከምንና፣ እስከ ሞትም
ሊያደርስ የሚችል ነው።

ዋናዎቹ የስኳር በሽታ ዓይነቶች፦
1-ኛ ዓይነት – በልጆችና በጉብሎች የሚገኘው
ነው። ድሮ “የልጆች ዓይነቱ” ስኳር በሽታ ተብሎ
ይታወቅ ነበር።
2-ኛ ዓይነት – ይህ በብዙ ሰው የሚገኘው ዓይነቱ
የስኳር በሽታ ሲሆን፣ “የኣዋቂዎች ስኳር በሽታ”
ተብሎ ይጠራ ነበር። ዛሬ ግን በልጆችም ኣዘውትሮ
ይታያል፣ ምክንያቱም የዛሬ ልጆች እጅግ ውፍረት፣
የሚዛን ክብደትና ኣለመንቀሳቀስን ስለሚያበዙ
ነው።
የእርግዝና ስኳር የሚበለውም በሽታ በኣንዳንድ
እርጉዞች ላይ ይገኛል።
የስኳር በሽታን እንዴት መቆጣጠር ይቻላል?
ስኳር በሽታ መድሓኒት የለውም፣ ግን ለመቆጣጠር
ይቻላል፦
· ጤና ምግብን በመብላት
· ሰውነትን በማንቀሳቀስ (ስፖርት በመሥራት)
· ሲጋራን በማቆም
· ኣስፈላጊ ሲሆንም ሕክምናን በማድረግ

የጤና ምግብ መመሪያዎች፦
በየቀኑ የተለያዩ ዓይነት ምግቦችን መብላት ይገባል፣
ምክንያቱም ለሰውነታችን የሚያስፈልጉ ቪታሚንና

ንጥረ-ነገሮችን እንድናገኝ ነው። የሚበላው የምግ
መጠን ግን ትንንሽ ይሁን፣ ቺፕስ፣ ኩኪስ፣
ከረሜላ፣ ቅቤ፣ ማርጀሪን፣ ማዮኔዝ፣ ጨው፣
የተጠበሱ ምግቦች፣ ኣይስ-ክሬም፣ ሸርቤት፣ ሶዳ።
በዘይት የተጠበሱትና ብዙ ቅባት ያለባቸውን ግን
በጣም ኣሳንሶ መብላት ይገባል።
በሌላ መንገድ ምግብን ጤና ማድረግ፦
· ያልተጣሩና ያልተነጠሩ፣ የሙሉ ገብስ ዳቦ፣
ጥቁር ሩዝና ሌላም ኣዝርእት መብላት።
· እሽት የሆኑ ኣታክልትና ፍራፍሬ
በመብላት።
· ፍሬዎችና የፍራፍሬ ጭማቂዎችን በመጠኑ
ኣሳንሰው በመግዛት።

· ሲጠብሱና ሲቀቅሉም ቅባትና ዘይት በጣም
በማሳነስ።
· እንዲያውም በመጥበሻ ላይ የሚረጨውን
ቅባት ከሌላው ዘይቶችና ቅባቶች ይልቅ
ኣዘውትረው በመጠቀም።
· ምግብን በዘይት ውስጥ ከመቀቀልና ከመጥበስ
ይልቅስ በውሃ መቀቀል፣ በእንፋሎት
ማብሰል፣ በደረቅ እሳትና በከሰል ላይ
መጥበስን ማዘውተር።
· ስባት ያልበዛባቸው የምግብ ዓይነቶችን
መምረጥ፡ (ዶሮ፣ ቀይ የበሬ ስጋ፣ ተርኪ፣)
ወተትም ስባት የሌለበት፣ የተናጠ (1% ወይም
2%) ዓይብና እርጎም እንዲሁ።

 

ስለ ስኳር በሽታ ተጨማሪ ማስረጃ በሚከተሉት
ማግኘት ይቻላል፦
www.aha.org
ww.cdc.gov
www.usda.gov
www.diabetes.org
ይህ ጽሑፍ ከሚከተሉት ምንጮች የተሰባሰበ ነው፦
American Heart Association
American Diabetes Association
The Centers for Disease Control
and Prevention (CDC)
Georgia State University, Department of
Geography and Anthropology
The U.S. Department of Agriculture (USDA)

 

Leave a Reply