ፎረፎርን ለማጥፋት ሊረዳዎት የሚችሉ 5 ነጥቦች

ፎረፎር በተለያዩ ውስጣዊና ውጫዊ ምክንያቶች ይከሰታል። በተለይም በጸጉር ቆዳችን ላይ የሚገኙ ነጭ የደም ህዋሳቶች ሲሞቱ ነው ፎረፎር የሚከሰተው።

ፎረፎር ፀጉር እንዲያልቅና እንዲበጣጠስ ከማድረጉም በላይ የጸጉር ውበትንና ቆዳን ይጎዳል።

ይሁን እንጂ በተለያዩ መንገዶች ፎረፎርን መከላከል ይቻላል።

1. በተለያዩ ሻምፖዎች እና ሳሙናዎች መታጠብ

2. እርጎ እና በርበሬ፦ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘው እርሾ በአንዳንድ የሰውነታችን ክፍሎች ላይ መጉረብረብ እና መንተብተብ ይፈጥራል። ለዚህም እንደ እርጎ ያሉ ጎጂ ያልሆኑ ባክቴሪያዎችን የሚይዙ የምግብ አይነቶችን መጠቀም አይነተኛ መፍትሄ ነው።

ሁለት ማንኪያ የደቀቀ በርበሬ እና 1 ኩባያ እርጎ በመደባለቅ ፀጉራችን የሚበቅልበትን ቆዳ መቀባት እና ከአንድ ስአት በኋላ መታጠብ ፎረፎርን ለማጥፋት ትልቅ ድርሻ እንዳለው ይነገራል።

3. እሬት (ኦሊ ቬራ)

እሬት ፎረፎርን ለመከላከል በተለይም በኢትዮጵያ ለበረካታ ዘመናት ስንጠቀምበት ኖረናል።
በፎረፎር የተገጎዳ ቆዳን እሬት መቀባት የሞቱ ህዋሳቶችን ከማስወገዱም ባሻገር ለፀጉር እድገት አይነተኛ ሚና እንዳለውም ይታመናል።

4. አፕል

አፕል ለፀጉር እድገት የሚረዳው ፕሮሳይኒዲን ቢ – 2 የተባለ የተፈጥሮ ንጥረ ነገር የያዘ መሆኑን ተከትሎ ጤናማ ፀጉር እንዲኖረን ያደርጋል።
ሁለት ማንኪያ የአፕል ጭማቂ ከሁለት ማንኪያ ውሃ ጋር በመቀላቀል መቀባት፤ ከዚያም ከ15 ደቂቃ በኋላ መታጠብ ፎረፎርን ለማጥፋት ብሎም የፀጉር እድገትን ለማፋጠን ይረዳል።

5. ዝንጅብል

ዝንጅብል ለሰውነት መጉረብረብ ወይም መመረዝ የሚያጋልጡ ነገሮችን የሚከላከሉ ንጥረ ነገሮች ይዟል።

ስለሆነም ዝንጅብልን በመላጥና በማድቀቅ ከሰሊጥ ዘይት ጋር በመደባለቅና የፀጉር ቆዳን በመቀባት ፎረፎርን መከላከል ይቻላል።

ለተጨማሪ መረጃ http://www.stylecraze.com/…/9-simple-home-remedies-for-dan…/

Leave a Reply