የሳንባ ነቀርሳ በሽታ Tuberculosis-TB

የሳንባ ነቀርሳ በሽታ Tuberculosis-TB

Source: Tedmedicine.org

የሳንባ ነቀርሳ ማይኮባክቴሪየም ትዩበርኩሎሲስ በሚባል ባክቴሪያ አማካይነት የሚመጣ በሽታ ነው ነቀርሳ የሚለው ቃል ካንሰርን ቢያመለክትም የሳንባ ነቀርሳ በሽታ ግን ካንሰር አይደለም ባክቴርያው በዋናነት የሚያጠቃው ሳንባን ቢሆንም ኩላሊትን አይምሮን አከርካሪንና ሌሎችንም የሰውነት ክፍሎች ያጠቃል

Tuberculosis-1

 

በሽታውን የሚያመጣው ማይኮባክቴሪየም ትዩበርኩሎሲስ የተባለው ባክቴሪያ ይህን ይመስላል

 

MTBCDC

እንዴት ይዛመታል ?

የሳንባ ነቀርሳ በሽታ የሚተላለፈው በአየር ውስጥ ነው ያ ማለት በሽታው ያለበት ሰው ሲያስል ሲያስነጥስ ወይም ሲናገር ባክቴሪያው አብሮ በመውጣት አየት ውስጥ ይቆይና በአቅራቢያው ያሉ ሰዎች ያንን አየር በሚስቡበት ጊዜ ባክቴሪያውን ወደሳንባቸው በማስበባት በበሽታው ይያዛሉ ባክቴሪያው በሰውነታችን ውስጥ አለ ማለት ግን የግድ በሽታው ይከሰታል ማለት አይደለም በዚህ ምክንያት ከቲቢ ጋር የተዛመዱ ሁለት አይነት ሁኔታዎች አሉ

  1. የተዳፈነ የቲቢ ኢንፌክሽን /Latent TB Infection/
  • ባክቴሪያው ሰውነታችን ውስጥ በሽታውን ሳያስከትል ዝም ብሎ ሊኖር ይችላል ይህም የሚሆነው ሰውነት በራሱ በሽታን የመከላከል ኃይል ባክቴሪያው እንዳያድግና እንዳይራባ ስለሚያግደው ነው
  • እንደዚህ አይነት ሰዎች ባክተሪያውን ወደሌላ ሰው አያዛምቱም ነገር ግን ባክቴርያው የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅም አሸንፎ ማደግ ከጀመረ የቲቢ በሽታን ያስከትላል

 

  1. የሳንባ ነቀርሳ በሽታ /TB disease/
  • ሰውነት በሽታን የመከላከል አቅሙ ሲደክምና ባክቴሪያው ለመራባት እድሉን ሲያገኝ ያን ጊዜ የሳንባ ነቀርሳ በሽታን ያስከትላል የተያዘውም ሰው የበሽታ ምልክቶችን ማሳየት ይጀምራል ሌሎች ሰዎችም የማስተላለፍ አቅም አለው
  • አንዳንድ ሰዎች ባክቴሪያው በሰውነታቸው ውስጥ ቢኖርም እስከመጨረሻው የባክቴሪያው ተሸካሚ ብቻ ሆነው ሳይታመሙ ይኖራሉ አንዳንዶች ደግሞ ወዲያውኑ ይታመማሉ ሌሎች ከተወሰነ ዓመት በሁአላ ሊታመሙ ይችላሉ
  • በተለያየ ምክንያት የሰውነታቸው የተፈጥሮ በሽታን የመከላከል አቅም ወይም ኢሚውን ሲስተም የተዳከመ ሰዎች በሽታውን በቀላሉ ያሳያሉ ለምሳሌ በኤች.አይ.ቪ ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች በቀላሉ የቲቢን በሽታ ያሳያሉ ምክንያቱም ቫይረሱ በዋናነት የተፈጥሮን የመከላከል ብቃት ስለሚያዳክም ነው

 

የበሽታው ምልክቶች

በሽታው ከሚያሳያቸው ምልክቶች ውስጥ ዋናዎች የሚከተሉት ናቸው

  • በትንሹ ከሶስት ሳምንት በላይ የሚዘልቅ መጥፎ ሳል
  • በደረት አካባቢ የሚሰማ የህመም ስሜት
  • ደም የቀላቀለ ወይንም ደም የሌለው አክታ
  • የድካም ስሜት
  • የምግብ ፍላጎት ማጣትና ክብደት መቀነስ
  • የብርድ ስሜት
  • ትኩሳት
  • በምሽት ጊዜ ማላብና ሌሎችም

 

ለቲቢ በሽታ መከሰት በቀላሉ የሚያጋልጡ ነገሮች

አንድ ሰው በባክቴሪያው ከተለከፈ በሁአላ የቲቢን በሽታን እንዲከሰት የሚያፋጥኑ የተለያዩ አጋላጭ ነገሮች አሉ ከነዚህም ጥቂቶቹ

  • በኤች. አይ. ቪ ቫይረስ መለከፍ
  • ከዚህ በፊት በቅርብ ጊዜ በባክቴርያው ተለክፎ እንደሆን ለምሳሌ ከሁለት ዓመት በፊት
  • ሌሎች የጤና እክሎች ካሉበት ለምሳሌ የስኳር በሽታ ያለበት ሰው ሰውነት ባክቴሪያውን በቀላሉ እንዳይዋጋ ያደርጉታል
  • የአልኮል መጠጥ ሱሰኛ መሆንና አደንዛጅ መድኃኒቶችን መጠቀም
  • ከዚህ በፊት የቲቢ በሽታ ኖሮበት በሚገባ ሕክምና ያላገኘ ሰው እና ሌሎችም ሁኔታዎች

 

በባክቴሪያው መያዛችንን እንዴት እናውቃለን

ባክቴሪያው በሰውነታችን ውስጥ መኖሩን ለማወቅ የሚረዱ ሁለት መንገዶች አሉ

  1. የቆዳ ላይ ቲቢ ቴስት /TB skin test/

 

  • ይህ መንገድ ትዩበርኩሊን የሚባል አነስተኛ መጠን ያለው ፈሳሽ በከንዳችን ቆዳ ውስጥ በመርፌ አማካይነት እንዲገባ ይደረጋል በሽተኛው ከ48-72 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ተመልሶ መምጣት አለበት በቆዳው ላይም አንዳች አይነት የለውጥ ምልክት እንዳለ ይታያል አበጥ ያለና ጠንከር ያለ ነገር ከታየ ምን ያህል እርዝመት እንዳለው ይለካል ብዙ ጊዜ ኖርማል የሚባለው 0.5 mm ነው ከዛ ከበለጠ ምርመራው ፖዘቲቭ ነው ባክቴርያው አለብን ማለት ነው
  • ከ 0.5mm ካነሰ ግን ምርመራው ኔጌቲቭ ነው ማለትም በባክቴሪያው የመያዛችን ዕድል እጅግ በጣም የመነመነ ነው እነኝህ ምርመራዎች ፍፁም አይደሉም

 

mantoux

 

  1. የደም ምርመራ /blood test/
  • ይህ ምርምራ ሰውነታችን ለባክቴርያው ምን አይነት ሪአክሽን እንዳሳየ የሚለካበት መንገድ ነው ፖዘቲቭ ከሆነ ባክቴሪያው አለብን ማለት ነው

 

እነኝህ ሁለት መንገዶች የሚረዱት ባክቴሪያው በሰውነት ውስጥ መኖር አለመኖሩን ለማወቅ ብቻ ነው ከላይ የጠቀስናቸው ሁለት አይነት የቲቢ ሁኔታዎች ማለትም የተዳፈነ ኢንፌክሽን ወይም የቲቢ በሽታ እንዳሉቡን ግን አይጠቁምም እነኝህ ሁለት ምርመራዎች ፖዘቲቭ ከሆኑ ሌላ ተጨማሪ ምርምራ ማድረግ ያስፈልጋል የደረት ኤክስ ሬይና የአክታ ምርመራ የቲቢ በሽታ እንዳለብን ለማወቅ ይረዳሉ

ሕክምና

የተዳፈነ የቲቢ ኢንፌክሽንን መታከም በሽታው እንዳይከሰት ይረዳል የቲቢ በሽታ ያለበት ሰው ግን በተለያዩ የመድሃኒት አይነቶች ይታከማል ሕክምናውም ከ6 እስከ 9 ወር ሊፈጅ ይችላል መድሃኒቱ በታዘዘው መጠን እና ለታዘዘልን ጊዜ በትክክል መውሰውድ በጣም አስፈላጊ ነው አለዛ ደግመን ልንታመም እንችላለን ባክቴሪያውም መድሃንቱን በቀላሉ ሊቋቋም ይችላል ተመልሶ ለማከምም አዳጋች ይሆናል ለህክምና ከሚታዘዙት መድኃኒቶች ጥቂቶቹ isoniazid (INH), rifampin (RIF), ethambutol (EMB), · pyrazinamide (PZA) ናቸው

Leave a Reply